የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን

Dire Dawa Administration Public Procurement and Property Authority

Message/መልዕክት

የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በሁሉም ግዥ ፈጻሚ የአስተዳደሩ ባለበጀት መ/ቤቶች በመንግሥት ግዥ አፈፃፀም የማስፈጸም አቅም በመገንባት፣ የግዥ አፈጻጸምና ንብረት አስተዳደር ውጤታማ በሆነ መንገድ የሚፈጸም ስለመሆኑ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ፣ በጥናት ላይ በመመርኮዝ ዘመናዊ እና ቀልጣፋ አሰራር ሥርዓት በመዘርጋት፣ በዘርፉ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና የአሰራር ማነቆዎችን ለመቅረፍ የሚያስችል ግልጽ፣ ቀልጣፋ፣ ፍትሐዊና ተጠያቂነት የተረጋገጠበት የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደርን ለማስፈን እየሰራ ይገኛል፡፡ባለስልጣኑ የህግ፣ የአሰራር እና የአደረጃጀት ማሻሻያ በማድረግ የሰው ሀይል አቅም በመገንባት እና አሰራሮችን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ፣ ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ሥርዓትና ቁጥጥርን በማጠናከር የመንግስት ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ጥቅም እንዲያስገኝ ለማስቻል እንዲሁም አፈጻጸሙ በአለም አቀፍ ተቀባይነት ባላቸው መስፈርቶች ሲመዘን ውጤታማነቱ በሚፈለገው ደረጃ እንዲሆን የባለስልጣኑን አገልግሎትና አስተዳደር የማሻሻያ ስራዎችንም እየሰራ ይገኛል፡፡በመሆኑም በዘርፉ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና የአሰራር ማነቆዎችን ለማስወገድ በየበጀት ዓመቱ ለመንግስት ግዥ የሚመደበው ከፍተኛ መጠን ያለው መዋዕለ ንዋይ ተመጣጣኝ የሆነ ፋይዳ እንዲያስገኝ እና በከፍተኛ ወጪ የተገዛው ንብረት ከብክነት በጸዳ መንገድ ሥራ ላይ የሚውልበትን የአሰራር ሥርዓት በማጠናከር ለሀገራዊ ሁለተናዊ ዕድገት አስተዋጽኦ ለማበርከት ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡በመሆኑም ለዚህ እቅድ መሳካት ሥራዎችን ህግና አሠራርን መሠረት በማድረግ በቅንጅትና በትብብር መስራት ወሳኝ በመሆኑ ባለስልጣኑ የሚመለከታቸው የመንግስትና የግል ባለድርሻ አካላት በተለይ የሁሉም ግዥ ፈጻሚ የአስተዳደሩ መንግስት መስሪያ ቤቶች አመራርና ፈጻሚዎች ዘርፉ በላቀ ደረጃ ውጤታማ እንዲሆን የሚጠበቀባችሁን ሚና እንድትወጡ ጥሪዬን እያስተላለፍኩ በባላስልጣኑ በኩል ለሰመረ የስራ ግንኙነትና ለውጤታማነት ያለሰለሰ ጥረት እንደሚደረግ ለማሳወቅ እወዳለሁ፡፡

Contact us

ddppa@gmail.com
+251122132

+251121166