የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን

Dire Dawa Administration Public Procurement and Property Authority

News Type : የ 9 ወራት መደበኛ ዕቅድ

Features : የድሬዳዋ አስተዳደር የ2015 ዓ.ም 9 ወራት የፕሮጀክቶችና መደበኛ ስራዎች ዕቅድ አፈፃፀምን ለመገምገም ያለመ የመስክ ምልከታ ቀጥሏል

News Details

የድሬዳዋ አስተዳደር የ2015 ዓ.ም 9 ወራት የፕሮጀክቶችና መደበኛ ስራዎች ዕቅድ አፈፃፀምን ለመገምገም ያለመ የመስክ ምልከታ ቀጥሏል ---------------------------------------- ከመንግስት ተቋማት ኃላፋች፤ ከፓርቲ አመራሮችና ከሚመለከተቻው ተቋማት የተውጣጡ ባለሞያዎች የያዘው በአራት ቡድን የተደራጀው የክትትል ቡድን በአስተዳደሩ ስር በሚገኙ ተቋማት ተይዘው እየተተገበሩ የሚገኙ ፕሮጀክቶችና መደበኛ ስራዎች ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም ላይ ይገኛል፡፡ በአራት ቡድን የተደራጀው ከድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የዘርፍ አማካሪዎች፣ ከድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ፣ ከብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አመራሮች እና ከድሬዳዋ አስተዳደር ፕላን ኮሚሽን የተዋቀሩ የሱፐርቪዥን ቡድኖች በአስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስት ተቋማትን የአፈፃፀም ጀረጃ ለማሻሻል የሚረዳ ክትትል እና ድጋፍ የማድረግ እንዲሁም የአፈፃፀም ግምገማ በማካሄድ ላይ ሲሆኑ በዛሬው እለትም በድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ፤ ስራ-አስኪያጅ ጽ/ቤት፤መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የ2015 ዓ.ም 9 ወራት የፕሮጀክቶችና መደበኛ ስራዎች ዕቅድ አፈፃፀምን ለመገምገም ያለመ ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን በመስክና የቢሮዎቹ ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ተደርገዋል።

Contact us

ddppa@gmail.com
+251122132

+251121166