የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን

Dire Dawa Administration Public Procurement and Property Authority

News Type : በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ

Features : የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን ከፌደራል የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን ከመጡ የስራ ሀላፊዎችና ከፍተኛ ባለሞያዎች ጋር ዉይይት አካሄደ፡፡

News Details

በመድረኩም የድህነት ቅነሳ ተኮር ተቋሞች ማለትም የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና ዉሀ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ፣የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የ2015 እና በ2016 በጀት አመት የWabe Based KPI System ሪፖርት የቀረበ ሲሆን  እንዲሁም በተሰሩ ስራዎች ላይ የታዩ የአመዘጋገብ ችግር፤የበጀት ልኬት ማነስ፤ እና ከስራዉ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ ጉድለቶች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተካሄዷል። በመጨረሻም በ2017 በጀት አመት በሚዘጋጀው ሪፖርት ዙሪያ ሁሉም ተቋሞች በሁሉም የግዢ ዘዴና በሁሉም የግዢ በጀት ምንጭ የፈፀሙትን ግዢዎች በዌብ ቤዝድ ኬፒአይ ሲስተም ስልጠና በወሰዱ የግዢ ባለሞያዎችና የአይስቲ ባለመያዎች ስራዉን በሲስተሙ ላይ በመመዝገብና በሀላፊ ደረጃ በማረጋገጥ ሪፖርቱን ለፌደራል ግዢና ንብረት ባለስልጣን በመላክ ባለስልጣኑም ወደ ሚመለከተዉ ገንዘብ ሚኒስቴርና ልማት አጋሮች በወቅቱ እንዲልክና እንዲሁም ከበጀት አፈፃፀም እና አመዳደብ ጋር ያለዉ ስራ ለአስተዳደሩ እንዲመደብ ለማስቻል በትኩረት መሰራት እንዳለበት በመድረኩ ተገልጿል። በሴና አብዲሳ ነሐሴ 13/2017 ዓ.ም

Contact us

ddppa@gmail.com
+251122132

+251121166