News Type : የዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም አተገባበር
Features : የተሸከርካሪ አስተዳደር ስርዓቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ንብረት አስተዳደደር ባልስልጣን በአስተዳደሩ ለሚገኙ ተቋማት የግዢ፤ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሮክቶሬት በተሸከርካሪ አስተዳደር የዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም አተገባበር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ አቶ ሀቢብ ፋራህ የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን ዳይሪክቶሬት በስልጠናው መክፈቻ ላይ እንዳሉት አብዛኛው የአስተዳደሩ ተቋማት የተሸከርካሪ አስተዳደር ስርዓት በርካታ እግሮች ያሉበት በመሆኑ ይህንን ችግር ለመቅረፍ እንዲቻል የተሸከርካሪ አስተዳደር ስርዓት ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን ተናግረው እስከ አሁን ድረስ 25 ተቋማት 300 ተሸከርካሪዎች ላይ የ G.P.S መሳሪያ የመግጠም ስራ መሰራቱን እና በቀጣይ በሌሎች ተቋማት ተሸከርካሪዎች ስራው እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡ በስልጣው መድረክ በአስተዳደሩ ተቋማት ተሻከርካሪዎች ዙሪያ የተዘጋጀው የዳሰሰ ጥናት ፁሁፍ እና b G.P.S መሳሪያ አጠቃቀም ዙሪያ የባለሞያ ገለጻ የቀረበ ሲሆን ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት መደረጉ ታውቋል፡፡ ጥር 9 / 2016
By logging in you agree to our Terms and Conditions and Privacy Policy