የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን

Dire Dawa Administration Public Procurement and Property Authority

News Type : የIMIS ተግባሪ ኮሚቴ መላው ሀገሪቱ የተወጣጡ ባለሙያዎች እና አመራሮች

Features : የIMIS ተግባሪ ኮሚቴ መላው ሀገሪቱ የተወጣጡ ባለሙያዎች እና አመራሮች

News Details

በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው IMIS የትግበራ ቡድን ከክልሎች የተውጣጡ IMIS አባላት መካከል የተደረገ ልምድ ልውውጥ ሲሆን በቀጣይ በከተማችን ድሬዳዋ የሚተገበረው የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት ለማጠናከር ግብዓት ያገኘንበት እና እንደ ድሬዳዋ አስተዳደር የመረጃ ስርዓቱን ለማስቀጠል በቀጣይ መደረግ ስላለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሁም ከክልሎች ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለብን የተረዳንበት መድረክ ነበረ ። በቀጣይ ከግንኙነት አግባብ ጋር በተያያዘ እንደ አቅጣጫ በተቀመጠው መሰረት IMIS ግሩፕ አባላት በ2015 ዓ.ም ግንኙነት በማጠናከርና የተለያዩ የማነቃቂያ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት የግሩፑ አባላትን በRedatam ሶፍትዌር ላይ ያላቸውን ግንዛቤ በይበልጥ ለማጠናከር ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው ተገንዝበናል። በአስተዳደር ደረጃ Redatam software አጠቃቀም በይበልጥ ለማስፋትና የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን ለማዘመን በየሴክተሩ ላይ ለሚመደቡ ለአዲስ አመራሮች ግንዛቤ በመፍጠር የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን ማስቀጠል እንደሚገባ የተገነዘብንበት መድረክ ነበረ የDire Dawa IMIS አባላት ከዚህ በፊት በልምድ ልውውጡ ያልተሳተፉ አባላት በሌሎች ስልጠናዎች ላይ እንዲሳተፉ እንደሚደረግና TOT ስልጠና የወሰዱ IMIS አባላት ስልጠና መስጠት እንዳለባቸው በልምድ ልውውጡ አቅጣጫ ተቀምጧል።

Contact us

ddppa@gmail.com
+251122132

+251121166