የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን

Dire Dawa Administration Public Procurement and Property Authority

News Type : የተቀናጀ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ተግባዊ እንዲሆን

Features : የተቀናጀ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ተግባዊ እንዲሆን

News Details

በድሬዳዋ አስተዳደር የተቀናጀ የመረጃ አያያዝን ስርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ በአስተዳደር ደረጃ ከሴክተር መ/ቤት የተወጣጡ የመረጃ ፣ ICT እንዲሁም የእቅድ ባለሙያዎችን በማሰልጠን እና ከዚህም ጎን ለጎን የድሬዳዋ IMIS አስተግባሪ ቡድን በማቋቋም ሰርቨሩን ለማስጀመር የመረጃ የማጠናከር ስራ በመሰራት ላይ ይገኛል። በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚታየውን ከመረጃ አያያዝ ችግር ይበልጥ ለማዘመንና ተጠቃሚው ህብረተሰብ በእጁ በሚገኘው ሞባይል ሆነ ኮምፒዩተር በየትኛውም አካባቢ ሆኖ በኢንተርኔት በመጠቀም መረጃዎችን ማግኘት እንደሚቻልም ተጠቅሷል። የተቀናጀ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ተግባዊ እንዲሆን የድሬዳዋ አስተዳደር ፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት ከUNFPA እና ESS ጋር በመተባበር ለIMIS ግሩፕ አባላት በRedatam ሶፍትዌር ላይ ይበልጥ አቅማቸው እንዲያጎለብቱ ጥሩ ተሞክሮ ካላቸው ክልል ጋር ልምድ እንዲወስዱ በማድረግ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን በመዘጋጀት ላይ ይገኛል። የድሬዳዋ አስተዳደርም ለስራው ልዩ ትኩረት በመስጠትም እንደሌሎች ክልሎች የአስተዳደሩን የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርዓትን ሰርቨሩን ለማስጀመር የIMIS ግሩፕ አባላት አስተግባሪ ቡድኑ መረጃ ልየታ ፣ መረጃዎችን በማጥራት እንዲሁም Area እና indicator code ስያሜ በተመለከተ የማነቃቂያ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል። የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት (IMIS) ድህረ -ገፁ ስራው ተጠናቅቆ በቅርቡ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፣ IMIS ግሩፑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተቋማት በተገኙበት ተመርቆ ለመረጃ ተጠቃሚ ህብረተሰብ ይፋ ሆኖ አገልግሎት ይጀምራል።

Contact us

ddppa@gmail.com
+251122132

+251121166