የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን

Dire Dawa Administration Public Procurement and Property Authority

News Type : የተቀናጀ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን ለማቀላጠፍ እንዲቻል አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተገለፀ።

Features : የተቀናጀ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን ለማቀላጠፍ እንዲቻል አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተገለፀ።

News Details

የተቀናጀ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን ለማቀላጠፍ እንዲቻል አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተገለፀ። ===========##============= በከተማችን ድሬዳዋ ተግባራዊ ለመሆን በዝግጅት ላይ የሚገኘው IMIS ድህረ-ገፅ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግ ልዩ ትኩረት እንደተሰጠ ተገልፆ የIMIS አባላትን ለማጠናከርና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ ፎረም መቋቋሙን ተገልጿል። የኤሌትሮኒክስ ላይብረሪ አገልግሎትን በተቋማት እንዲሰጥና ተግባራዊ እንዲሆን አስፈላጊ ግብዓቶችን በሟሟላት ስራዎች ለመስራት እንዲቻል በእንቅስቃሴ ላይ እንደሆነ ተገልጿል። የድሬዳዋ IMIS ፎረም ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ በRedatam ሶፍትዌር ላይ ስልጠና የወሰዱ የእቅድ፣የመረጃና ICT ባለሙያዎች የተመሰረተ ሲሆን ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ በየወሩ በመገናኘት የሚመክር ሲሆን የማስፈፀሚያ እቅድ በማዘጋጀት ስራው እንደሚሰራ ተገልጿል። በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚታየውን የመረጃ አያያዝና ተደራሽነት ችግር ለመቅረፍ   ''IMIS ድህረ-ገፅ'' አይነተኛ ሚና እንዳለው ተገልፆ በድሬዳዋ አስተዳደር አገልግሎት ሲጀምር ከመረጃ አያያዝና ተደራሽነት ጋር በተያያዘ የሚታዩትን ክፍተቶች ከመሙላቱም በላይ መረጃዎችን በተቀላጠፈ መንገድ ለመረጃ ፈላጊው ተደራሽ ለማድረግ ምቹ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥር ታምኖበታል። የIMIS አስተግባሪ አባላትም በፔጁ ላይ የተሰራውን ስራ ጨምሮ የተደራጀውን የሴክተር መረጃዎችን በመገምገም ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሆነ ተገልፆ የሰርቨርና  ከቴሌ ጋር የማገናኘት ስራ ከተጠናቀቀ በኃላ ድህረ-ገፁ ይፋ ሆኖ ለመረጃ ፈላጊ ህብረተሰብ ተደራሽ ይሆናል። #የተቀናጀ_የመረጃ_አስተዳደር_ስርዓት_ለሁሉም

Contact us

ddppa@gmail.com
+251122132

+251121166