የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን

Dire Dawa Administration Public Procurement and Property Authority

News Type : ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን

Features : ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን

News Details

የድሬዳዋ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ “ሴቶችን እናብቃ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ!” በሚል መሪ ቃል የዘንድሮውን የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አክብረዋል። ዕለቱን አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ግርማ ተሰማ ባስተላለፉት መልዕክት ሴቶች በሀገር ልማት ያላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያሉባቸውን ተግዳሮቶች በማስወገድ በህብረተሰቡ የአስተሳሰብ ለውጥ በማምጣት ረገድ ጠንክረው መስራት ይጠበቅባቸዋል በማለት መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን ኃላፊውም አክለው ሴቶች በሰላምና በዴሞክራሲ ግንባታ ላይ ያላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እና የፆታ እኩልነት በማረጋገጥ በሀገራችን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የልማት ተሳትፎዎች ላይ ያላቸውን ድርሻ ለማሳደግ በሁሉም ዘርፍ መሰራት እንዳለበት ጠቁመዋል:: የቢሮው የስርአተ ፆታና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ባለሞያ ወ/ሪት ያምሮት ካሳሁን እንደተናገሩት በየአመቱ የሚከበረው ማርች 8 እ.ኤ.አ በ1900ዎቹ ተንሰራፍቶ በነበረው ግፍ፣ ጭቆናና በደል ምክንያት ሴት እናቶቻችን እህቶቻችን ለመብታቸው የታገሉበትና ነፃነታቸውን ያስከበሩበት የትግል ውጤታቸውን የምንዘክርበት እንዲሁም በሴቶች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ንቅናቄ በመፈጠሩ ሴቶች ዝቅተኛ የስራ ሰዓት፤ የተሻለ ክፍያ እና የመምረጥ መብታቸው በማስጠበቅ ረገድ ባደረጉት እንቅስቃሴ ቀኑ ታስቦ ይውላል ብለዋል። በቢሮው የፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ኮሚሽን የሶሺዮ ኢኮኖሚና ስነ ህዝብ ቡድን መሪ ወ/ሮ ዘነቡ ሰይድ እንደገለፁት ቀኑን  ከመዘከር ባለፈ ለአገር ግንባታ የሴቶች ሚና የጎላ በመሆኑ በተሰማራንበት የስራ መስክ ሁላችንም በጋራ መቆምና በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ አድሎዎች እንዳይኖሩ መታገል ይኖርብናል ብለዋል።

Contact us

ddppa@gmail.com
+251122132

+251121166